የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ አቻው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደርጋል።

124
ባሕርዳር : መጋቢት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የአቋም መለኪያ ጨዋታው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ
22 ሰኢድ ሀብታሙ
18 ሽመልስ በቀለ
2 ሱሌማን ሀሚድ
15 አስቻለው ታመነ
16 ያሬድ ባዬ
14 ሚልዮን ሰለሞን
6 ጋቶች ፓኖም
8 አማኑኤል ዮሐንስ
5 ታፈሰ ሰለሞን
19 ከነዓን ማርክነህ
7 አቤል ያለው
ጨዋታው ዋልያዎቹ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ አቋማቸውን እንዲፈትሹ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ዋልያዎቹ ከጊኒ ጋር ላለባቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከነገ በስቲያ ወደ ሞሮኮ ያቀናሉ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አራት ከግብጽ፣ ማላዊ እና ጊኒ ጋር የተደለደለች ሲሆን እስካሁን ሁለት ጨዋታ አድርጋ 3 ነጥብ በማግኘት በአንድ የግብ ክፍያ ምድቡን እየመራች ትገኛለች።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!