የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ሕብረት በድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ያጋጥሙ የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያደረገውን ጥረት አደነቀ።

0
13

የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ሕብረት በድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ያጋጥሙ የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ
ምርጫ ቦርድ ያደረገውን ጥረት አደነቀ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 16/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ሕብረት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ለመታዘብ በርካታ
ታዛቢዎችን ምርጫው በተካሄደባቸው የተለያዩ አካባቢዎች አሰማርቶ እንደነበር ገልጿል።
ዛሬ በሰጠው መግለጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሰላማዊ ኾኖ መጠናቀቅ መቻሉን መታዘቡን አውስቷል።
ሕብረቱ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በርካታ ጠንካራ ጎኖች እንደነበሩት ገልጾ፤ በተለይም የምርጫ ቦርድ በሂደቱ ሲያጋጥሙ የነበሩ
ክፍተቶችን ለመሙላትና ወቅታዊ ምላሽ ለመስጠት ያደረገውን ጥረት አድንቋል።
መራጮችም ድምጽ ለመስጠት በትዕግስት መጠበቃቸው መልካም እንደነበር አውስቷል።
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሂደቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው መመልከቱን ሕብረቱ መግለጹን
ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በየምርጫ ጣቢያዎች ሴቶች ንቁ ተሳትፎ እንደነበራቸው የገለጸው ሕብረቱ፤ የምርጫ አስፈጻሚዎች ለአካል ጉዳተኞች፣ ሕጻናት
ለያዙ እናቶች፣ ለአረጋውያንና ሌሎች አካላት ቅድሚያ በመስጠት ማስተናገድ መቻላቸው በሂደቱ ከታዩ መልካም ነገሮች መካከል
እንደሚጠቀስ አመልክቷል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here