የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች፡፡

0
73

ባሕር ዳር፡ ጥር 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች በፈጸመው ወረራ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ የሚውል የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጋለች፡፡

የቤተ ክርስቲያኗ ሀገረ ስብከት በቅርቡ ባደረገው የሥራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ ላይ በአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች በተፈጸመው ወረራ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ መምከሩን ያወሱት የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተ ክርስቲያን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ቄስ ኢሳያስ ኦሻ 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደሷልም ብለዋል፡፡

ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ አብያተክርስቲያናት የሚገኙ ምዕመናን ወገኖቻቸውን ከሃብት እስከ ጸሎት ለመደገፍ ዝግጁ ናቸው ያሉት ቄስ ኢሳያስ ክልሉ ሙሉ በሙሉ ከጉዳቱ እስኪያገግም እና ተጎጂዎች እስኪጽናኑ ቤተ ክርስቲያኗ ከጎናችሁ ናት ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ያደረገችውን የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ የተረከቡት የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጅዓለም ድጋፉ ወቅቱን የጠበቀ እና አጋርነትን የሚገልጽ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ ከወረራው ጋር ተያይዞ ከ11 ሚሊየን ሕዝብ በላይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልገዋል ያሉት ኮሚሽነር ዘላለም ተቋማት፣ ድርጅቶች፣ ማኅበራት፣ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/