የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያሉበትን ክፍተቶች በማስተካከል ወደ ተሻለ አሠራር እየገባ መሆኑን ገለፀ።

0
236

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያሉበትን ክፍተቶች በማስተካከል ወደ ተሻለ አሠራር እየገባ መሆኑን ገለፀ።
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 13/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በሀገር አቀፍ
ደረጃ በምጣኔ ሀብት እቅድ አዘገጃጀትና ራዕይ ቀረፃ፣ የፋይናንስ ሒሳብ አስተዳደር፣ ንግድ ሥራ አመራር፣ ገበያ ፍለጋ፣ ሰው ሀብት
አስተዳደርና በፖሊሲ ጉዳይ አቅማቸውን በመገንባት ዕውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው የሚያስችል ለአምስት ቀናት የሚቆይ
የመጀመሪያው ዙር ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ በባሕር ዳር እየተሰጠ ይገኛል።
ከፍኖተ ሠላም ከተማ የመጡት ወይዘሮ ዞማነሽ አንለይ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫው ለሥራቸው ቅልጥፍና እገዛ ሊያደርግ
እንደሚችል ተናግረዋል። ሆኖም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የብድር አገልግሎት ቢያመቻችም የብድር አለቃቀቅ ላይ ችግር
እንደሚስተዋል ወይዘሮ ዞማነሽ አስረድተዋል።
ከባሕር ዳር ከተማ በአሽከርካሪ መገጣጠም ኢንተርፕራይዝ የተሠማሩት አቶ አበበ ይስማው፣ ሥራቸውን ሲሠሩ የነበረው
በልምድ መሆኑንና ስልጠናው ይህን ክፍተት ሊሞላላቸው እንደሚችል ጠቁመዋል። የሒሳብ አያያዝ፣ የሥራ ዕቅድን አውጥቶ
ስለመሥራትና ማሠራት፣ ስለሠራተኛ አያያዝና አጠቃቀምን በተመለከተ ከግንዛቤ ማስጨበጫው በቂ ግንዛቤ እንዳገኙ
ተናግረዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫው በተለይ ኢንተርፕራይዞች ሠራተኞቻቸውን ከመቀነስ በዘለለ እንዴት አድርገው ማሠራት እንዳለባቸው፣
ሳይንሳዊና በመርህ ላይ የተመሠረተ አሠራር እንዲኖር ጠቃሚ መሆኑን አቶ አበበ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የባሕር ዳር ዲስትሪክት ተወካይ ሥራ አስኪያጅ ስንታየሁ ልንገረው፣ የባንኩ ተበዳሪዎች በብዙ ሚሊዮን
የሚገመት ንብረቶችን ስለሚያስተዳድሩ እንዲሁም በስራቸው በርካታ ቁጥር ያለው ሠራተኛ ያላቸው በመሆኑ የእነዚህን
ኢንተርፕራይዞች አሠራር ክፍተት ለመሙላት የግንዛቤ ማስጨበጫው እንደተዘጋጀ አስረድተዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫው ልማት ባንኩ ለኢንተርፕራይዞቹ የብድር አገልግሎት ከመስጠቱ በፊት አመለካከቱ የተቀየረና በቂ
ስልጠና ያገኘ ባለሀብት ለማፍራት ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።
“አለማቀድ ውድቀትን ማቀድ ነው” ያሉት ተወካይ ሥራ አስኪያጁ ባለ ሀብቱ የዕቅድ ዝግጅትን ምንነት ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል
ተብለዋል።
“ብዙን ጊዜ ባለ ሀብቶች ስህተታቸው ትርፍ የሚያገኙት የሠራተኞቻቸውን ደመወዝ ወይም ጥቅማጥቅም በመቀነስ
ይመስላቸዋል፤ ነገር ግን ለሠራተኞቻቸው ተገቢውን ክፍያ በመፈጸም ለሥራ እንዲተጉ ማድረግ ለአንድ ፕሮጀክት ዕድገት ወሳኝ
ሚናን ይጫወታል። አሁን እየሰጠን ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ባለ ሀብቱ ስለ ፕሮጀክቱ በቂ ዕውቀትና ክህሎት እንዲኖረው
ያስችለዋል” ብለዋል።
ባንኩ የነበረበትን ክፍተቶች በማረም ወደ የተሻለ አሠራር እየገባ ነው ያሉት ተወካይ ሥራ አስኪያጁ ከባንኩ መሻሻል ባለፈ ደግሞ
የደንበኞችን ክፍተት መሙላት ነው ብለዋል።
ባንኩ ተጨማሪ የብድር አቅርቦትን ለመስጠት መጀመሪያ ከሰጠው የብድር አገልግሎት የሚመጥን ሥራ ተሠርቶ ማየት
እንደሚፈልግ ተወካይ ሥራ አስኪያጁ አስገንዝበዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫው በተመሳሳይ ቀናት ባሕር ዳር ከተማን ጨምሮ በሀገሪቱ በሰባት ከተሞች በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ
ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here