የኢሕአዴግ ምክር ቤት የፖርቲውን ውሕደት አጸደቀ።

0
77

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ምክር ቤት የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከቀናት በፊት የመራለትን የፓርቲውን ውሕደት አጸደቀ።

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ዛሬ ማካሄድ በጀመረው ስብሰባ ነው ውሕደቱን የተመለከተውን ሐሳብ ያጸደቀው።

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በውሕድ ፓርቲ ፕሮግራም ላይ ዝርዝር ውይይት እና ክርክር በማካሄድ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆ ረቂቁን ለኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲቀርብ ወስኖ ነበር።

በተመሳሳይ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በተዋሐደው የብልጽግና ፓርቲ ሕገ ደንብ ላይ ተወያይቶ እንዲጸድቅ ለኢሕአዴግ ምክር ቤት እንዲመራ መወሰኑ ይታወሳል።

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ የምክር ቤቱን ስብሰባ ውሎ አስመልክተው ለኢብኮ እንደተናገሩት ምክር ቤቱ ባካሄደው ስብሰባው በፓርቲው ውሕደት ዙሪያ ተወያይቱ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቀዋል።

ምክር ቤቱ ውሕደቱን በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ነው አቶ ፍቃዱ የተናገሩት።

የፌዴራል ሥርዓቱን በማጠናከር፣ የብሔርና የሀገር አንድነትን፣ የግለሰብና የቡድን መብትን በማስታረቅ፣ ከመደብ ትግል በመውጣት ለመታገል ውሕድ ፓርቲው እንደሚመሠረት ተናግረዋል።

ነገ የፓርቲውን ሕገ ደንብ በተመለከተ ውይይት አድርጎ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here