የአፍሪካ ከፍተኛው ችግር የእውቀት ብርሀን ማጣት እንደኾነ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ተናገሩ፡፡

0
64

የአፍሪካ ከፍተኛው ችግር የእውቀት ብርሀን ማጣት እንደኾነ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ተናገሩ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 19/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ከፍተኛው ችግር የእውቀት ብርሀን ማጣት እንደኾነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ የአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማዕከል በሚል ስያሜውን በይፋ ዛሬ በቀየረበት እና አዲስ ያስገነባውን የአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማዕከል ባስመረቀበት ሥነ-ስርዓት ላይ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አፍሪካ የሰለጠኑ፣ የበቁ እና የተሻሉ መሪዎችን ትፈልጋለች ለዚህ ደግሞ ይህ ተቋም ሚናውና አበርክቶው የጎላ ነው ብለውዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ”የአፍሪካን ሁለንተናዊ እድገት እየጎተተው ያለው ነገር ድንቁርና በመኾኑ ይህ አካዳሚ የያዘውን ተልኮ ከተወጣ ከኛም አልፎ ለአፍሪካ መሰረት የሚጥል ነው“ ብለዋል።

በእውቀት የደረጀ ትውልድና አህጉር ለመፍጠር እና አፍሪካን በእውቀት ነጻ ለማውጣት ይህ አካዳሚ ድርሻው የጎላ እንዲኾን ይሠራል ብለዋል።

አካዳሚው አሁን የተደራጀበትን አቅም እና የካሪኩለም ዝግጅት በሙሉ አቅሙ በመተግበር የሚጠበቅበትን አህጉራዊ ግዴታ እንዲወጣም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አደራ ጥለዋል። የሥራ ኀላፊዎችም በአካዳሚው የአረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።

ዘጋቢ፡-ጋሻው ፋንታሁን-ከአዲስ አበባ

ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here