የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፤ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ይፋዊ ጥሪ ማቅረቡን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

116

መስከረም 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር ለመፍታት መንግሥት ሰኔ 20/2014 ዓ.ም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሰብሳቢነት የሚመሩት በአጠቃላይ ሰባት አባላት ያሉት የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል።

የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፤ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ይፋዊ ጥሪ ማቅረቡን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ መንግሥት ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን አቋሞች የጠበቀ ሆኖ ተገኝቷል ያለው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ብቻ እንዲሆንና ያለ ቅድመ ሁኔታእንዲደረግ መንግሥት አቋሙን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል ብሏል።

ግጭቱን ለመፍታት መንግሥት ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ ርምጃዎች ለመውሰድ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ያወሳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፥ መንግሥት ይህንኑ አጠናከሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J