የአፍሪካ ኅብረት ምስረታውን ሲያከብር ለአፍሪካውያን ሰላም፣ ደህንነት እና እድገትን ለማምጣት በመትጋት መኾን ይገባዋል ሲሉ የኅብረቱ ሊቀመንበር ገለጹ።

15

አዲስ አበባ: ግንቦት 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ኅብረት የተመሰረተበትን 60 ኛ ዓመት በኅብረቱ ግቢ እያካሔደ ነው።

በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሃማት የጋራ ልማት እና ሰላምን ማምጣት አስቦ የተጀመረው ኅብረቱ ብለዋል። ይህን አሳክቶ ዛሬ አጓጊውን የ2063 አጀንዳ ለማሳካት የሚተጋበት ጊዜ ላይ ደርሷልም ነው ያሉት። ዛሬ ይህንን ምስረታ ስናስብ የምናደርገው በኔልሰን ማንዴላ አዳራሽ ነው ስለዚህም የመስራች አባቶችን አላማ ለማሳካት በመሥራት መኾን ይገባል ብለዋል።

በአፍሪካ ወንድሞች መካከል በሚፈጠረው አለመግባባት በርካታ ችግሮች አሉ፤ የአህጉሪቱ ዜጎችም ለስደት፣ መፈናቀል እና ርሀብ ይዳረጋሉ። ይሁንና የሚፈጠሩ ችግሮችን ምክንያታቸውን ከስሩ በማወቅ በራሳችን መፍትሔ ማምጣጥ አለብን ብለዋል።

እንደኮሚሽን ሊቀመንበሩ ገለጻ ዛሬ በዓሉን ስናከብር በልዩ ሁኔታ አጀንዳ 2063ን ለማሳካት በመትጋት መሆን ይገባል ነው ያሉት። አፍሪካ ከምትገለጽበት የኃላ አካሔድ ወደተሻለ መንገድ ለማምጣት በመትጋት መሆን አለበት ሲ ሉ ተናግረዋል።

ዓለም በተለያየ ክፍፍል በሚንቀሳቀስበት በዚህ ጊዜ አፍሪካ ያላትን የጂኦ ፖለቲካ አስፈላጊነት አጎልብታ አቅሟን ማሳደግ አለባት ሲሉ ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን