የአፍሪካ መሪዎች የአሜሪካን የመካከለኛው ምሥራቅ የሠላም እቅድ ሳይቀበሉት ቀሩ፡፡

0
100

ባሕር ዳር: የካቲት 02/2012 ዓ.ም (አብመድ) በ33ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ እየተሳተፉ የሚገኙት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡትን የመካከለኛው ምሥራቅ የሠላም እቅድ ሳይቀበሉት ቀርተዋል፤ እንዲያውም አውግዘውታል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ከፍልስጤም ጎን መሆናቸውንም አሳይተዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽነር ሊቀ መንበር ሙሣ ፋኪ ማህማት እንደገለፁት በአውሮፓውያኑ ጥር የተዋወቀው የትራምፕ እቅድ በርካታ የመንግሥታቱ ድርጅትና የአፍሪካ ኅብረት የመፍትሔ ሐሳቦችን የሚጥስ ይዘት እንዳለው ተናግረዋል፡፡
‹‹ዓለም አቀፍ ምክክር ሳይደረግበት የተዘጋጀ እቅድ ነው›› ብለዋል ከሚሽነሩ፡፡ በፍልስጤም ሕዝብ መብቶች ላይ የተረማመደ እቅድ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ የፍልስጤማውያን ጉዳይ ሁሌም በአፍሪካ ሕዝብ ልብ ውስጥ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡
የኅብረቱ ሊቀ መንበርና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራምፎሳ ደግሞ ረቂቁን ደቡብ አፍሪካ በአፓርታይድ ጊዜ ከተዘረጋላት የቁጥጥር ሥርዓት ጋር እንዳነጻጸሩት አፍሪካኒውስ አስነብቧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here