የአፍሪካ ሕብረት 40ኛው የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬ ይጀምራል፡፡

164

ጥር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ሕብረት 40ኛዉ የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ የሕብረቱ አባል ሀገራት ሚኒስትሮችና የአህጉሩ ልዩ ልዩ ተቋማት ኃላፊዎች በሚገኙበት ዛሬ ይጀምራል።

በ40ኛው የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የምሥራቅና ደቡብዊ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ዋና ጸሐፊን ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዴታዎች አዲስ አበባ ገብተዋል።

የምክር ቤቱ ስብሰባ “የአፍሪካ አህጉርን የሥርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፣ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማትን ማፋጠን” በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2022 መሪ ቃል ላይ የሚመክር ሲሆን ከጥር 28 -29/2014 ዓ.ም ለሚካሄደው 35ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።

የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት በሕብረቱ አባል ሀገራት የጋራ ፍላጎት የሆኑ የፖሊሲ ጉዳዮችን የሚያስተባብርና ውሳኔ የሚሰጥ ነው።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን አባላት በመምረጥ የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ እንዲያጸድቅ የሚያደርግ ሲሆን ከቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማኅበረሰቦች፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ፣ ሌሎች የአፍሪካ ተቋማትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ያለው ትብብርና ትስስር እንዲጠናከር የማስተዋወቅ ሥራ ያከናውናል።

የአፍሪካ ሕብረትና የአፍሪካ አጋሮች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን በማዘጋጀት በአህጉሪቷ የሰላም፣ ጸጥታና ሌሎች የጋራ አጀንዳዎች ረቂቅ የውሳኔ ሐሳቦችን ያቀርባል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ምክር ቤቱ በአፍሪካ ሕብረት ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትን አፈጻጸምና ሕብረቱ እ.አ.አ በ2021 ያካሄዳቸውን ስብስባዎች የተመለከቱ ሪፖርቶችን ያደምጣል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/