የአፍሪካና ሩሲያ የኢኮኖሚ ትብብር ማስተባበሪያ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፈተ።

0
298

ባሕር ዳር: የካቲት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ እና የሩሲያ የኢኮኖሚ ትብብር ማስተባበሪያ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት (አፍሮኮም) ጽሕፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ከፈተ፡፡

በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የሩሲያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል ሴናተር ኢጎር ሞሮዞቭ፣ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጀኒ ተረሂን እና የሃይማኖት አባቶችን የወከሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የበላይ ኀላፊ ብጹዕ አቡነ አረጋዊ እና የመንግሥት ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ሴናተር ኢጎር እንዳሉት፥ ማዕከሉ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በንግድ እና በኢንቨስትመንት እና በተለያዩ የኢኮኖሚ መስኮች ለሚያደርጉት ግንኙነት የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

አምባሳደር ኤቭጀኒ ተረሒን በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሁለትዮሽ ግንኙነት ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት ቢኖራቸውም በንግዱና በኢኮኖሚው ዘርፍ የጎላ ትስስር ሳይፈጥሩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።

የጽሕፈት ቤቱ መከፈትም ሀገራቱ ለሚያደርጉት የንግድና የኢኮኖሚ ትብብር የመሰረት ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል ነው ያሉት። ፋብኮ እንደዘገበው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/