የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአማራ ክልል 40 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ አደረገ።

0
103

አዲስ አበባ: የካቲት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአማራ ክልል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምግብና ለወደሙ ተቋማት ደግሞ የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉም 40 ሚሊየን ብር የሚያወጣ መኾኑ ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሕዝቡን በማቋቋም ሂደቱ አብረን እንሠራለን ብለዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የአዲስ አበባ ሕዝብ ማንም ኢትዮጵያዊ ሲነካ የማይወድ መኾኑ በሚያደርገው ተከታታይ ድጋፍ አረጋግጧል ነው ያሉት። ለተደረገው ድጋፍም ምሥጋና አቅርበዋል።

የተደረገው ድጋፍ ከንፍስ ስልክ ላፍቶ እና ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተሰበሰበ ነው ተብሏል።

ዘጋቢ:- ዳንኤል መላኩ-ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/