የአሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን አጀንዳ ሕዝቡ ከሠራዊቱ ጋር በመኾን ሊያከሽፍ እንደሚገባ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ አሳሰቡ።

0
95

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ከሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርን ከሸባሪው ቡድን ነጻ ካደረገ በኋላ ማኅበረሰቡ ያለስጋት መደበኛ ሥራውን እየከወነ እንደሚገኝ ተሳታፊዎቹ አንስተዋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ በብሔረሰብ አስተዳደሩ እያከናወነ ያለው የልማት እንቅስቃሴ የበለጠ የሠራዊቱን ሕዝባዊነት ያሳየ እንደኾነም ነው ተሳታፊዎቹ ያነሱት። ይኹን እንጅ በሽብር ቡድኑ የተያዙ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ አካባቢዎችን ነጻ በማድረግ የተፈናቀለው ሕዝብ ወደ መደበኛ ሕይወቱ እንዲመለስ ሠራዊቱ ሕዝባዊ አደራነቱን እንዲወጣ ተሳታፊዎቹ ጠይቀዋል።

በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሚገኘው ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ የሽብር ቡድኑ አሁንም ለዳግም ወረራ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አሸባሪው ቡድን የሚሰነዘረውን ማንኛውም ትንኮሳ ለመቀልበስ አኹንም ሠራዊቱ ዝግጁ መኾኑን ገልጸዋ።

ሕዝቡ ለሠራዊቱ ከዚህ በፊት ያደርግ የነበረውን አጋርነት በማጠናከር የሽብር ቡድኑን አጀንዳ ሊያከሽፈው ይገባል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/