የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በትግራይ ክልልና አዋሳኝ አካባቢችዎች ቁጥጥር እንደሚያካሂድ ገለጸ።

0
186
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በትግራይ ክልልና አዋሳኝ አካባቢችዎች ቁጥጥር እንደሚያካሂድ ገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 08/2013 ዓ.ም (አብመድ) ቦርዱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት የታሰሩ ግለሰቦችን የማሳወቅ፣ የሚወሰዱ እርምጃዎች ኢ-ሰብአዊ እንዳይሆኑ የመቆጣጠር፣ እርምጃዎች ተገቢ አለመሆናቸውን ሲያረጋግጥም ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የማሳወቅ፣ የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለህግ የማቅረብና የማራዘም ውሳኔ ላይ ሀሳብ የመስጠት ተግባር ተሰጥቶት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጁ ቁጥር 1228/2013 የተቋቋመ ነው።
ቦርዱ በሰጠው መግለጫ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ከትግራይ ክልልም በተጨማሪ ታራሚዎች በሚኖሩባቸው አዋሳኝ የአፋርና አማራ ክልሎች ቁጥጥር እንደሚያደርግ ገልጿል።
የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ የከፋ ችግር የሚከሰትባቸው አካባቢዎች እየተለዩ በቦታው በመገኘት ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው ተናግረዋል። ቦርዱ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እንዳይፈጸም ቁጥጥር ያደርጋል ተፈፅሞ ሲገኝም ፈፃሚ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ለፍርድ ያቀርባል ብለዋል።
ቦርዱ የተሰጠውን ህገመንግስታዊ ሀላፊነት ለመወጣት የሚያስችሉ ስልቶችን አዘጋጅቶ ወደ ስራ እንደገባም አብራርተዋል።
ማህበረሰቡ ጥቆማዎችን ማድረስ የሚችልበት አሰራር መዘርጋቱንም ተናግረዋል።
ማህበረሰቡ በስልክ ቁጥር 0111544181 /239980 እና በነፃ መስመር 8557 ላይ በመደወል ጥቆማ መስጠት ይችላል ብለዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ለታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ 7 አባላት ያሉት መርማሪ ቦርድ መሰየሙ ይታወሳል።
ዘጋቢ፦ ዘመኑ ታደለ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here