የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማደረግ በትኩረት እየሠራ መሆኑን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ተቋም የፓዌ ግብርና ማዕከል አስታወቀ።

0
181

ባሕር ዳር፡ መስከረም 26/2012 ዓ/ም (አብመድ) ማዕከሉ የ2011/2012 የመኸር ወቅት የእርሻ ሥራ እንቅስቃሴ የአኩሪ አተር ሰብል የኩታ ገጠም አመራረት አርሶ አደሩንና ባለ ድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ የመስክ ምልከታ አካሂዷል።

ማዕከሉ ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ በሰብል ልማት፣ በእንስሳት ሀብት ልማት፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በእንስሳት መኖ እና በሌሎችም ዘርፎች ትኩረት አደርጎ እየሠራ እንደሚገኝ የምርምር ማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ተሻለ ተናግረዋል።

ማዕከሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአኩሪ አተር የምርምር ማዕከል ነው፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሰፋፊ ኩታ ገጠም ሥራዎችን በተለያዩ ሰብሎች በተለይም ደግሞ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትና የውጭ ምንዛሬ ሊያስገኙ የሚችሉ እና የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና ያላቸውን ሰብሎች ወደ አርሶ አደሩ እያሠራጨም ነው፡፡

በዋናነት በቴክኖሎጅ የታገዘ የአኩሪ አተር ምርትን ማኅበረሰብ ዓቀፍ አገልግሎት መሠረት ባደረገ መልኩ በሀገሪቱ አዳዲስ ዝርያዎችን በማውጣት፣ በማላመድና በማስተዋወቅ በኩል አበራታች ሥራዎችን መሥራቱን የተናገሩት በማዕከሉ የአኩሪ አተር ተመራማሪ አቶ ደረሰ ወልዴ ናቸው።

በምርምር የተደገፈ የግብርና ሥራን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ገልጸው ማኅበረሰቡ ሁሉን አቀፍ ግብዓቶችን ተጠቅሞ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን ሰፊ ግንዛቤ ለቀጣይ መሥራት እንደሚገባ በምልከታው የተገኙት በክልሉ ግብርና ቢሮ የኤክስቴሸን ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ፀሐይ አዳሙ አሳስበዋል።

በመስክ ምልዕከታው የተሳተፉ አርሶ አደሮችም ከእርሻ ማሳዎች በተለያዩ የቴክኖሎጅ ዉጤቶች የለሙ የሰብል ዓይነቶችን ተሞክሮ በመቅሰም ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

የምርምር ማዕከሉ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንና በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ለሥነ ምኅዳሩ ምቹ የሆኑ ሰብሎችን በማለመድ ይታወቃል።

መረጃውን ያደረሰን የመተከል ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here