የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር) በደቡብ ጎንደር ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ተመለከቱ።

31
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርዕሰ መሥተዳድሩ የተመራው ከፍተኛ የአመራሮች ቡድን በደቡብ ጎንደር ዞን ስማዳ ወረዳ እየተሠራ ያለውን የአጓት ውኃ የመስኖ ፕሮጀክት ተመልክቷል።
የአጓት ውኃ የመስኖ ፕሮጀክት በ2008 ዓ.ም ተጀምሮ በተለያየ ምክንያት ሲጓተት የቆየ ነው። በዚህ በጀት ዓመት የክልሉ መንግሥት ያለውን ችግር ገምግሞ በመፍታት ወደ ሥራ እንዲገባ በማስቻሉ ፕሮጀክቱ በተሻለ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር) ፕሮጀክቱ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲኾን፤ ፕሮጀክቱ በተለያየ ችግር ሲጓተት የቆየ መኾኑን ገልፀው፤ በዚህ በጀት ዓመት የክልሉ መንግሥት ለፕሮጀክቱ በሰጠው የትኩረት አቅጣጫ መሰረት ሥራው በጥሩ ኹኔታ እየሄደ ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱም ከ2 መቶ ሄክታር በላይ እንደሚያለማና በርካታ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ነው የተናገሩት።
የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ሥራው በፍጥነት እንደጠናቀቅ የማሽነሪ እቃዎች እንዲጨመሩ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የማሽነሪ እቃዎች ተጨማሪ የገቡ መኾኑንና ለሥራው እንቅፋት የሚኾኑ ነገሮችን በማስገድ ሥራው ተጠናቆ ለማኅበረሰቡ አገልልግሎት እንዲሰጥ የክልሉ መንግሥት ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም ጨምረው ተናግረዋል።
የፕሮጀክቱ ተቋራ
May be an image of 2 people, people standing and outdoorsጭ የኾነው የአማራ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዘመነ ፀሀይ በበኩላቸው፤ እንደተቋራጭ ፕሮጀክቱን በየጊዜው በመገምገምና የጎደሉ ነገሮች እንዲሟሉ በማድረግ ሥራው በተሻለ ደረጃ እየተከወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በቀጣይም የጎደሉ ነገሮች እንዲሟሉና ሥራው በታቀደለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ተቋራጭ ድርጅቱ በትኩረት የሚሠራ መኾኑን ገልፀዋል።
የፕሮጀክቱ አማካሪ መሃንዲስ ኢንጅነር መንግሥቱ አራጌ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ 62 ነጥብ 3% የደረሰ መኾኑን ገልፀው የፕሮጀክቱ ሥራ እንዲፋጠን በየደረጃው ያለው አመራር ባደረገው ክትትልና ድጋፍ ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ እየተሠራ ነው ብለዋል።
አመራሩ ፕሮጀክቱን በሚጎበኝበት ወቅት የማሽነሪ ችግር እንዳለ በመግለፃችን አኹን ላይ ችግሩን የሚፈቱ በርካታ ማሽነሪዎች መግባታቸውን ጨምረው ገልፀዋል።
በቀጣይም የፕሮጀክቱ ሥራ እንዲፋጠን የግብዓት አቅርቦት እንዲሟላና ተጨማሪ ማሽነሪዎች እንደገቡ ኢንጅነር መንግሥቱ ጠይቀዋል።
የደቡብ ጎንደር ዞን መስኖና ቆላማ መምሪያ ኃላፊ አቶ በልስቲ ፍስሀ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቱ ተጀምሮ ለበርካታ አመታት የካሳ ክፍያ ባለመኖሩ ምክንያት ሥራው ቆሞ መቆየቱን ገልፀው መስኖና ቆላማ ቢሮና በየደረጃው ያለው አመራር ባደረገው ርብርብ የፌደራል መንግስት 32 ሚሊዮን ብር ካሳ ከፍሎ ፕሮጀክቱ በተገቢው መንገድ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ተሎ እንዲጠናቀቅ እና የጎደሉ ነገሮች እንዲሟሉ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራር በየጊዜው ክትትልና ድጋፍ እያደረገ መኾኑንም ነው የገለፁት።
በጉብኝቱ ላይም የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር) ጨምሮ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አቶ ይርጋ ሲሳይ እንዲሁም የክልል፣ የዞንና የወረዳው አመራሮች ተገኝተዋል። መረጃው የደቡብ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!