የአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር አልማ ከራያ ቆቦና ዋግኽምራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡

0
58

የአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር አልማ ከራያ ቆቦና ዋግኽምራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአልማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አራጋው ታደሰ ማኅበሩ ከልማት ሥራዎች ባሻገር በተለያዩ ምክንያቶች ለሚፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ማኅበሩ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጭ በማድረግ 327 ኩንታል ፊኖ ዱቄት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ እና ምላሽ ቡድን መሪ አቶ መሐመድ ሰይድ የአልማ ድጋፍ ተፈናቃዮቹን ለማገዝ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አለሙ ይመር በዞኑ ከ150 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የአልማ ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑንና የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የሚመለከታቸው አካላትም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ ቀጣይነት እንደሚኖረውም የአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር (አልማ) አስታውቋል፡፡

ዘጋቢ፡- ሀያት መኮነን – ከደሴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here