የአማራ ሕዝብን ለእልቂት እየዳረጉ ያሉ መዋቅራዊ ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈቱ የምሁራን መማክርት ጉባኤ አሳሰበ፡፡

0
219

ሰኔ 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከሰሞኑ በምስራቅ ወለጋ የተከሰተውን የንጹሃን ጥቃት አስመልክቶ የምሁራን መማክርት ጉባኤ መግለጫ አውጥቷል፡፡
መማክርት ጉባኤው በመግለጫው የፌደራል እና የክልል መንግስታት በአማራነት ላይ የተዘራውን የተዛባ ምስል ለማስተካከል ባለመፈለጋቸው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚኖረው ሕዝብ መዋቅራዊ በሆነ መልኩ የፖለቲካ ውክልና ተሳትፎ እንዳይኖረው በመደረጉ ለተከታታይ ጥቃት እየተዳረገ ነው ብሏል፡፡
የትኛውንም የኅብረተሰብ ክፍል በተሟላ ሁኔታ የማይወክሉ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፓርቲ አመራሮች እና ልሂቃን ተጨባጭ እውነታውን እና የሀገሪቱን ሙሉ የታሪክ ኩነቶች ወደ ጎን በመተው ከረጀም ዓመታት ጀምሮ ለየራሳቸው ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ሲሉ ነገሮችን ሁሉ አዛብተው ሲያቀርቡ ቆይተዋል ብሏል፡፡ በመሆኑም በዚህ የተዛባ ምስል ምክንያትም ከሁነቶቹ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው ንጹሃን በየጊዜው ተሳድደዋል ነው ያለው መግለጫው፡፡
መግለጫው ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ አሁንም ድረስ ያለማቋረጥ በሚያሳዝን ሁኔታ ንጹሃን ህጻናት፣ አረጋዊያን እና ሴቶች ሳይቀር ሆን ተብሎ በሚቀሰቀስ የጥላቻ እርምጃ በርካቶች በግፍ ተገድለዋል ብሏል፡፡ መሰል ጥፋቶች አሁንም ድረስ አልቆሙም ያለው መግለጫው በመንግስት፣ በፖለቲካ ሃይሎች፣ በሃይማኖት ተቋማት፣ በሲቪክ ማሕበራትም ሆነ በሌላ አካል ችግሩን ከመሰረቱ ለመቅረፍ እርምጃ ሲወሰድ አልታየም ነው ያለው፡፡
ጥፋት አድራሾች የሚፈልጉትን ጥፋት በፈለጉት ቦታ እና ጊዜ በፈለጉት አካል ላይ ፈጽመው መውጣት እንደሚችሉ እየታየ ነው ያለው መግለጫው መንግስት አጥፊዎችን ተከታትሎ እርምጃ ሲወስድም አልታየም ነው ያለው፡፡ ከጊዜ ጊዜ ችግሮች የሻሻላሉ ተብሎ ቢጠበቅም ከመባባስ እና አሳሳቢ ከመሆን የተለየ ነገር እንዳልታየም አመላክቷል፡፡
የተሳሳተው የሃሰት ትርክት እንዲስተካከል እና በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚኖር የአማራ ሕዝብ የፖለቲካ ተሳትፎ እንዳይኖረው በመደረጉ ከጥቃት ራሱን መከላከል እንዳልቻለም የምሁራን መማክርት ጉባኤው መግለጫ ያወሳል፡፡
የአማራን ሕዝብ ለእልቂት እየዳረጉ ያሉት መዋቅራዊ ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈቱ ምሁራን መማክርት ጉባኤው ጠይቋል፡፡
መግለጫው ከዚህ ቀደም የተፈጸሙ የግፍ ጥቃቶች ፍትህ ሳያገኙ ከሰሞኑ በንጹሃን አማራዎች ላይ የተካሄደው የጅምላ ግድያዎች የኦሮሚያ ክልል እና የፌደራል መንግሥት ጥፋቶች ናቸው ብሏል፡፡
የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል መንግስታት ለደረሰው ጉዳት ቀጥተኛ ጥፋተኛ በመሆናቸው ኅላፊነታቸውን ባልተወጡ አካላት ላይ ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ጠይቋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/