የአማራ ልማት ማኅበር በጎንደር ከተማ አየር ጤና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለ ሁለት ፎቅ ሕንጻ ግንባታ አስጀመረ።

0
84
የአማራ ልማት ማኅበር በጎንደር ከተማ አየር ጤና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለ ሁለት ፎቅ ሕንጻ ግንባታ አስጀመረ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ቤት ግንባታው በአልማ እና በዳሽን ቢራ ፋብሪካ ትብብር ነው የሚከናወነው፡፡ ትምህርት ቤቱም በ16 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ወጭ ይገነባል ተብሏል፡፡
የጎንደር ከተማ አልማ ቅርንጫፍ የአልማ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አደራጀው አላበ የትምህርት ቤት ግንባታው የትምህርት ቤቱን ደረጃ ለማሻሻል መሠረት እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ ይሄ ጅማሬ መሆኑን እና በቀጣይም አልማ ጎንደር እንድትለማ ለማድረግ እንደሚሠራ ነው የተናገሩት።
አልማ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ እየሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የዳሽን ቢራ ፋብሪካ የማኅበራዊ ዘርፍ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ እንዳልካቸው አበበ ፋብሪካው በተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ ተሣታፊ መሆኑን አንስተው የአየር ጤና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ለተማሪዎች ምቹ የመማር ማስተማር ሂደትን እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
ፋብሪካው የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማስጠቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ተናግረዋል።
የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሞላ መልካሙ ከዓለም ጋር ተወዳዳሪ እና ቀዳሚ ለመሆን የተማረ ማኅበረሠብን መገንባት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል ።
የዳሽን ቢራ ፋብሪካ እና አልማ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት ለመገንባት ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል። በትምህር ቤቱም የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር ተካሂዷል።
ዘጋቢ፡- ደስታ ካሳ-ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here