የታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንቲስት ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ።

78
የታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንቲስት ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ።
ባሕር ዳር:መጋቢት 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንቲስት ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።
ዶክተር ተወልደ ብርሃን የተወለዱት ከአባታቸው ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከእናታቸው ወይዘሮ መዓዛ ወልደ መድህን የካቲት 12 ቀን 1932 ዓ.ም በትግራይ ክልል ዓድዋ ከተማ አቅራቢያ ባለች “አዲ-ሰላም” የገጠር መንደር ነው።
በብዝሃ ሕይወት ጥናትና ምርምር ለሀገራቸውና ለዓለም የሚጠቅም አስተዋጽኦ በማበርከታቸው በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችንም አግኝተዋል።
በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ላደረጉት ምርምር እ.ኤ.አ 2000 “ራይት ላይቭሊሁድ አዋርድ” እና እ.ኤ.አ በ2006 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጠውን “ቻምፒዮንስ ኦፍ ዘ ኧርዝ” ካገኟቸው ሽልማቶች መካከል ይጠቀሳሉ።
ታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንቲስት ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ሕይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!