የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ኢትዮጵያዊ ዳኞች እንዲመደቡለት ጠየቀ፡፡

0
245

የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ኢትዮጵያዊ ዳኞች እንዲመደቡለት ጠየቀ፡፡

የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በአንድ ተጠባቂ የቱኒዚያ ሊግ ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያዊያን ዳኞች እንደሚደቡለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌሬሽንን በድብዳቤ ጠይቋል፡፡

በአፍሪካ እግር ኳስ በጠንካራ ተፎካሪነታቸው ከሚታወቁት ቡድኖች መካከል የቱኒዚያ እግር ኳስ ቡድኖች ይጠቀሳሉ፡፡ የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በቱኒዚያ ሊግ ጥር 6 ቀን 2012ዓ.ም የሚጠበቀውን ኢስፔራኒስ ዲ ቱኒዝ እና ኤቷል ዶሳሂል የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ ዓለም አቀፍ ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማና ሁለት ዓለም አቀፍ ረዳት ዳኞችን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መርጦ እንዲመድብለት ለፌደሬሽኑ በላኩት የትብብር ደብዳቤ መጠየቁን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በድህረ ገጹ አስታውቋል፡፡ በቱኒዚያ ሊግ በ2019/2020 የውድደር ዘመን ኢስፔራኒስ ዲ ቱኒዝ በ25 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኤቷል ዶሳሂል በ23 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

በታርቆ ክንዴ