የተፈጥሮ አደጋ እያደረሰ ያለውን ችግር አስመልክቶ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት መሪዎች ውይይት አደረጉ፡፡

0
74

ባሕር ዳር፡ መስከረም 07/2013ዓ.ም (አብመድ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የተፈጥሮ አደጋ እያደረሰ ያለውን ችግር አስመልክቶ ከፌዴራል እና የክልል መንግሥታት መሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውውይቱ በርካታ ክልሎችን ያጠቃውን የተፈጥሮ አደጋ አስመልክቶ መንግሥት የወሰዳቸውን ርምጃዎች በተመለከተ ከክልል መሪዎች ጋር መወያዬታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል።

‘‘በሀገሪቱ ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ቢከሰትም፣ ምንም ዓይነት የሞት አደጋ አለመድረሱ መልካም ነው’’ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በአካባቢዎቹ ደርሶ አስፈላጊውን ድጋፍ እየሰጠ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በተከታታይ በተደረጉ ውይይቶች በሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የሚቀርቡ ዕርዳታዎችን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ቀጣይ መቀመጡንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

አልፈው አልፈው የሚነሡትንና የዜጎችን ሕይወትና ንብረት እየነጠቁ ያሉትን የፀጥታ እክሎች አስመልክቶም መወያዬታቸውን አንስተዋል። ‘‘በተለይም በድንበር አካባቢ የሚፈጠሩት ክሥተቶች፣ የለውጡን ጉዞ ለማደናቀፍ በሚሹ ቡድኖች የሚቀናበሩ ናቸው’’ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በእነዚህ ግጭቶች ውስጥ ተሳታፊ የሆኑትን ሁሉ በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሚመራው ተልእኮ እንደሚኖርም ገልጸዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የታገቱት 29 ሰዎች እንዲለቀቁ ጥረት ላደረጉ አካላት ምሥጋና አቅርበዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here