የተዛቡ ሃሳቦች አንድነታችንን በሚያስጠብቅ መልኩ እንዲታረሙ የወጣቶች አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ።

21
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ
ባሕር ዳር:መጋቢት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የስልጠና መድረክ “በወጣቶች አቅም የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ይረጋገጣል” በሚል መሪ ሀሳብ ከመጋቢት 3 – 11/2015 ዓ.ም በባሕርዳር ከተማ ሲካሄድ ቆይቷል። በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የተለያዩ የክልል እና የፌደራል የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀንበር (ዶ.ር) ኢትዮጵያን ወደተሻለ እድገት እና ብልፅግና ለማድረስ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። ወጣቶች ሀገር ተረካቢ በመኾናቸው በሀገራችን ውስጥ የሚታዩ ተግዳሮቶችን በቅንጅት ለመፍታት መጣር አለባቸው ብለዋል።
ዶክተር ጌታቸው የተዛቡ ሀሳቦች እንዲታረሙ እና አንድነታችንን በሚያስጠብቅ መልኩ እንዲስተካከሉም የወጣቶች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ወጣቶች የተዛቡ ሀሳቦችን በማረም ከቀደምቶቻችን የተቀበልናትን ሀገር የመጠበቅ እና ከነክብሯ የማስቀጠል ኀላፊነት አለባቸው ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!