የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ተገለጸ።

0
44

ባሕር ዳር: የካቲት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢነርጂ ልማት ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልጉ የሀገሪቱ አምባሳደር ገለጹ።

የውኃና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋና ሌሎች የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ሉዊዝ ኤድዋርዶ እና ከባልደረቦቻቸው ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ በኢነርጂ በተለይ የሶላር የሃይል አማራጭን ለማልማት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ ፍሎራይድን ጨምሮ የተበከለ ውሃን ማከሚያ ቴክኖሎጂዎችን በተመለከተ በጋራ ለመስራት መክረዋል።

በተጨማሪም ብራዚል የእንቦጭ አረምን በማስወገድ ረገድ ያለውን ጥሩ ተሞክሮና ቴክኖሎጂ ለመጋራት ተወያይተዋል።

ሚኒስቴሩ እና ኤምባሲው በቅርበት ስራዎችን ለመስራት እንዲያስችላቸውም ተወካይ መድበው ለመስራት መስማማታቸውን ከውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/