ባሕር ዳር፡ ግንቦት 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውይይቱን የጀመረው በቅርቡ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡት ለፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባል ለአቶ ግርማ የሺጥላ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው።
ኮሚቴው በሚኖረው ቆይታ በሀገራዊ እንዲሁም በፓርቲያዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ለውይይት በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ የጋራ ግምገማ በማድረግም መላውን ሕዝብ በማሳተፍ የሚሳኩ የብልፅግና ጉዞ ትልሞች ላይ እንደሚመክር ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!