የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎበኙ።

127

ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያዘጋጀው “ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2015″ን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተዘጋጀውን ኢትዮጵያ ታምርት ሀገር አቀፍ ኤክስፖ መርቀው መክፈታቸው ይታወሳል።

በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር ዓባይ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች ተገኝተዋል። በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ያለው “ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2015” በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።

በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 124 አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን አቅርበዋልም ተብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!