የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ 5 ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የ4 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡

0
149
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ 5 ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የ4 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡
በምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሱትም፡-
1. አቶ አድጎ አምሳያ
2. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ
3. አቶ ግርማ መኒ
4. አቶ አረጋ ባልቢድ ናቸው፡፡
ምክር ቤቱ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የቀረቡትን የ4ቱን የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
በመተከል ዞን በንጹኃን ዜጎች ላይ በደረሰው ሞት፣ ጉዳትና መፈናቀል እጅግ ማዘናቸውን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በመተከል ዞን በንጹኃን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ የማያመው እና የማያወግዝ ሊኖር አይገባም ብለዋል፡፡
በተፈፀመው ጭፍጨፋ አመራር የተሳተፈበት መሆኑን የጠቆሙት የምክር ቤቱ አባላት፣ ዞኑን ከመረጋጋት አልፎ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ በድርጊቱ በተሳተፉ አካላት ላይ የተጀመረው የህግ የበላይነት የማስከበር ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ያኮረፉ አካላት፣ ህዝቦች እንዳይረጋጉና በሠላም እንዳይኖሩ እያደረጉ በመሆኑ ከመንግስት ቁርጠኛ እርምጃ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡
እናቶች፣ ህጻናትን ጨምሮ በተፈፀመው ጭፍጨፋ ለተፈናቀሉ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ፣ አካባቢውን አረጋግቶ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መሥራት ይገባልም ብለዋል፡፡
የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታደለ ተረፈ፣ በመተከል ዞን በዜጎች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝና ሊደገም የማይገባው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ ተጨማሪ ሞት፣ መፈናቀልና ጉዳት እንዳይከሰት የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ማሳሰባቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here