የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ ከዓለም አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች።

420
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ

ባሕር ዳር: መጋቢት 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ በ9 ሜዳሊያ ከዓለም አንደኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቃለች፡፡

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የሩጫ ዓይነቶች በሁለቱም ፆታ 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ማምጣት ችለዋል፡፡

ይህ ውጤትም የኢትዮጵያ ከፍተኛው የአለም የቤት ውስጥ ውድድር ውጤት ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አሜሪካ እና ስዊዘርላንድ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2008 በተደረገው 12ኛው የቫሌንሽያ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 4 ወርቅ፣ 1 ብር፣ 1 ነሃስ ስታመጣ በ2018 በተካሄደው 17ኛው የበርሚንግሃም የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ደግሞ 4 ወርቅ፣ እና 1 የብር ሜዳሊያ ማምጣት መቻሏን ከፌደሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/