የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ያልተገባ ጫና የሚቃወም ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው።

99

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ ሁሉም ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው።

ሰልፉ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ያልተገባ ጫና የሚቃወም ሲሆን፤ ሰልፉ መነሻውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አድርጎ የአሜሪካ መንግስት መቀመጫ ወደ ሆነው ‘ካፒቶል ሂል’ መድረሻውን ያደረገ ነው።

በሰልፉ ላይ በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እየተሳተፉ ነው።

ሰልፈኞቹ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ያልተገባ ጫና የሚቃወሙ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

ሰልፈኞቹ አሸባሪው ሕወሓት እየፈጸማቸው ያሉ አሰቃቂ ድርጊቶች እና የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ዙሪያ የሚያሰራጯቸውን ሐሰተኛ መረጃዎችንም አውግዘዋል።

ሰላማዊ ሰልፍ “የበቃ” ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻ አካል ሲሆን፤ ሰልፉን የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማኅበር ዋሺንግተን ግብረ ኀይል ከተለያዩ ተቋሞችና ሀገር ወዳጆች በጋራ ያዘጋጁት ነው።

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation