ባሕር ዳር: ግንቦት 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በዛሬ እለት የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ቀሪ የግንባታ ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
በመረሐ ግብሩ ላይ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማእረግ የማኅበራዊ ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስዩም መኮንን፣ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳን ጨምሮ ሌሎች የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዝቅተኛውን የፊፋ መስፈርት ማሟላት የሚያስችለውን የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃ ከፋለ የግንባታ ሂደቱ አበረታች ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ቀሪ ሥራዎችን በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ የሰው ኃይልና አስፈላጊ ግብአት ማሟላት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ የስታዲየሙ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቅቆ ተፈላጊውን አገልግሎት እንዲሰጥ የምናደርገውን ክትትል አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!