የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄዱ የኢትዮጵያን የዲጅታል ስኬት ለማሳየት መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ተገለጸ።

0
78

ባሕር ዳር፡ ሕዳር 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አንቶኒዮ ፔድሮ ጋር በኒጀር ኒያሚ ተወያይተዋል፡፡

አንቶኒዮ ፔድሮ የዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አሥተዳደር ጉባኤ በፈረንጆቹ ሕዳር 28 ቀን 2022 በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል።

መድረኩ የኢትዮጵያን የዲጅታል ስኬት ለሌሎች ለማሳየት መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ጠቁመው ፤ በከፍተኛ ደረጃ እንድትወከልም ጠይቀዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ስለግብዣው አመስግነው መንግስት የመድረኩን መካሄድ እንደሚያግዝ ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J