የ”በቃ” ንቅናቄ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ተካሄደ

91

የ”በቃ” ንቅናቄ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ተካሄደ።

ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የ’በቃ’ ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻ አካል የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ በአውስትራሊያ ፓርላማ ፊት ለፊት ተካሄደ።

ሰልፈኞቹ ባሰሙት መፈክር የምዕራቡ ዓለም አንዳንድ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ያልተገባ ጫናና ጣልቃ ገብነት አውግዘዋል።

የአንዳንድ ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኀኖች በኢትዮጵያ ላይ የሚያሰራጯቸውን ሐሰተኛ ዘገባዎችን እንዲያቆሙና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች የፈጸማቸውን በደሎች እንዲያወግዙ ጠይቀዋል።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ድርጊቶች በዓለም አቀፍ ወንጀል የሚያስጠይቅ እንደሆም አስገንዝበዋል።

‘ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ጎን ነን፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሕዝብ ድምጽ የተመረጠውን መንግሥት ማክበርና እውቅና መስጠት አለበት’ የሚሉና ሌሎች ‘የበቃ’ እንቅስቃሴ መልዕክቶች በሰልፉ ላይ ተላልፈዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላትና የኢትዮጵያ ወዳጆች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሰልፉን ያዘጋጁት በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት መሆናቸው ተገልጿል።

‘የበቃ’ ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻ አካል የሆኑ ሰላማዊ ሰልፎች ዛሬ በዴንማርክ ኮፐንሀገንና በግሪክ አቴንስ ይካሄዳሉ።

‘የበቃ’ ወይም #NoMore እንቅስቃሴ አፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያ፣ ሰሜን አሜሪካና ኦሺኒያ አህጉራትን አዳርሷል።

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation