የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የ33ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሌኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ።

2017
የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የ33ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሌኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ።
ባሕር ዳር፡ ጥር 03/2013 ዓ.ም (አብመድ)
አሸባሪው ትህነግ በሀገርና በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ክህደት በመመከት የጁንታውን ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ሥር ለማዋል እና የህግ ማሥከበር ዘመቻው በሥኬት እንዲጠናቀቅ ያሥቻሉት የ33ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሌኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥረዓት ተፈጸመ።
አሸባሪው ትህነግ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገርና በመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመውን ክህደት ተከትሎ ኮሌኔል አለምነው በተወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የቅራቅርን ግምባር በመምራትና በመዋጋት የትህነግ ህልም እንዲከሽፉ አድርገዋል።
በህይወት ታሪካቸው እንደተገለጸው የማይጸብሪን ግንባር በመምራትና አካባቢውን ከጠላት ነፃ በማድረግ የሕግ ማስከበር ዘመቻው እንዲሳካ ኀላፊነታቸውን በጀግንነት የተወጡ የጦር መሪ ናቸው።
የውትድርና ህይወትን በ17 ዓመታቸው የጀመሩትና ለ36 ዓመታት በትግል የቆዩት ኮሎኔል አለምነው በ51 ዓመታቸው በሀገረ ሠላም የጁንታውን ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከጠላት ጋር በተካሄደ ውጊያ ነው ህይወታቸው ያለፈው።
የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በጀግንነት ባህልና በክብር በደቡብ ጎንደር ዞን በንፋስ መውጫ ከተማ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ጥር 03/2013 ዓ.ም ተፈጽሟል።
የ5 ልጆች አባት የሆኑት ኮሎኔል አለምነህ ደርግን በማስወገድ፣ በኢትዬ ኤርትራና በሠላም አስከባሪነት ዘመቻዎችና በተለያዩ የትግል ቦታዎች ጀግንነታቸውን ያሳዩ ፅኑ የጦር መሪ እንደነበሩ ነው የተገለጸው።
ዘጋቢ:– ወንዳጥር መኮንን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ