የሲዳማ ክልል ለመከላከያ ሠራዊት የ45 ሚሊዮን ብር የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

0
45

የሲዳማ ክልል ለመከላከያ ሠራዊት የ45 ሚሊዮን ብር የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለመከላከያ ሠራዊት የ45 ሚሊዮን ብር የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በመከላከያ ሚኒስቴር የሕብረት ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ የፋይናንስ ሥራ አመራር ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄነራል አስረስ አያሌው ክልሉ የሽብር ቡድኑን ትህነግ ለማስወገድ እየተፋለመ ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሕዝባችንን ከጎናችን አደርገን ሀገራችንን ለማመስ የሚቋምጠውን የጽንፈኛ ጁንታ ላይበቅል እንነቅላለንም ነው ያሉት፡፡

የሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ አቶ አሸናፊ ኤሊያስ በበኩላቸው ለሠራዊታችን ደጀን በመሆን 221 በሬ፣ 216 በግ እና 204 ፍየል ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማም በእናቶች የተዘጋጀ ስንቅ በአጠቃላይ 15 ሚሊዮን ሚያወጡ በአይነት እና 30 ሚሊዮን በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እንዳደረጉ መናገራቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here