የሩሲያ ትልቁ የመከላከያ ኮንትራክተር እየበረረ መተኮስ የሚችል ባለድሮን ክላሽንኮቨ መስራቱን አስታወቀ።

0
283

የሩሲያ ትልቁ የመከላከያ ኮንትራክተር እየበረረ መተኮስ የሚችል ባለድሮን ክላሽንኮቨ መስራቱን አስታወቀ።

ባለድሮኑ ክላሽንኮቭ እየተኮሰና እየበረረ በአየር ላይ ለ40 ደቂቃዎች ያህል የመቆየት አቅም አለው ተብሏል።

ባለ23 ኪሎግራሙ በራሪ ክላሽንኮቭ ባለፈው ዓመት የአዕምሮዋዊ ንብረት ባለቤትነት መብት ተሰጥቶታል።

በሞስኮ የአቬይሽን ተቋም ውስጥ መሳሪያውን ዲዛይን ያደረገው ግለሰብ እንደተናገረው በራሪ የሆነ ኢላማውን መምታት የሚችል መሳሪያ እውን ማድረጋቸውን ተናግሯል።

የአቬይሽን ተቋሙ እንደገለጸው መሳሪያው መጀመሪያ የሳተውን ኢላማ በራሱ ጊዜ ፈልጎ ማግኘት እንደሚችልም ገልጸዋል።

መሳሪያውን በተመለከተ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የተለቀቁ ሲሆን፥ በተመሳሳይ ሰዓት እየበረረ ሲተኩስ ታይቷል።

የመሳሪያውን ይፋ መሆን አስመልክቶ መገናኛ ብዙኀንን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

 

ምንጭ፦ ሞስኮታይምስ