አዲስ አበባ፡ ጥር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገር አቀፍ የፈጠራ ባለሙያዎችና የጀማሪዎች (startups ) የውይይት መድረክ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።
በዝግጅቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) እንዳሉት የልማት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ፣ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት፣ ለኢኮኖሚና አጠቃላይ ለሀገር ደኅንነት ፈጠራና የቴክኖሎጂን አቅምን ማሳደግ ዘመኑ የሚፈልገው መሰረታዊ ነገር ነው።
የሥራ ፈጣሪዎችና ጀማሪዎች ያላቸውን አቅም ተጠቅመው ለሀገር ልማትና እድገት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
የሥራ ፈጣሪዎች የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች ተቋቁመው ባላቸው ዕውቀት ራሳቸውንና ሀገራቸውን ለመጥቀም ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባቸውም ተናግረዋል።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ለሥራ ፈጣሪያዎችና ጀማሪዎች ለማበረታታት ለአሠራር የማይመቹ የሕግ ማዕቀፎችን ማሻሻል ጨምሮ አስፈላጊ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ባዘዘው መኮንን – ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/