የምርጫው በሰላም መጠናቀቅ የኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ እንደማይደራደሩ ማረጋገጫ መሆኑ ተገለጸ።

0
33

የምርጫው በሰላም መጠናቀቅ የኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ እንደማይደራደሩ ማረጋገጫ መሆኑ ተገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 16/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ)
ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ መጠናቀቁ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጉዳይ እንደማይደራደሩ በተግባር ያሳየ መሆኑን
ምሁራን ገለጹ።
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር አቶ ጀማል ሰይድ ለኢዜአ እንደገለጹት ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና
ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግስትና ምርጫ ቦርድ ያደረጉት ቅደመ ዝግጅት የሚደነቅ ነበር፡፡
ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ያገኙትን ነጻነት ተጠቅመው ፕሮግራምና ዓላማቸውን ብቻ ለህዝብ ለማስተዋወቅ ያደረጉት ጥረትና
ትብብር የዲሞክራሲ ምህዳሩን ያሰፋ ነው ብለዋል፡፡
ምርጫ ቦርድም ገለልተኛ ሆኖ ለሚስተዋሉ ክፍተቶች የሚወስደው ፈጣን የማስተካከያ እርምጃ የተቋሙን አቅምና የዴሞክራሲ
ፍላጎት አጉልቶ በማሳየቱ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ሀገርና ህዝብን አስቀድመው በሰላም እንዲጠናቀቅ ማድረጋቸውን እንደሚያደንቁ የገለጹት ምሁሩ፤
በህዝብ ድምጽ የሚያሸንፈው ፓርቲ ለቀጣይ የህዝብ ጥያቄዎች መዘጋጀት ይኖርበታል ብለዋል።
እርሳቸውም ያለ ማንም አስገዳጅ ለሚፈልጉት ፓርቲ ድምጻቸውን በነጻነት መስጠታቸውን ጠቅሰው፤ ምርጫው ሰላማዊ፤
ተዓማኒና ነጻ ለመሆኑ ምስክር ነን ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የሰላም፤ ዲሞክራሲና ልማት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር አልዩ ውዱ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በሴራ
ፖለቲከኞች ሳይታለል ሰላምና አንድነቱን ጠብቆ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ አድርጓል ብለዋል።
በዚህም ለሀገሩ ያለውን ፍቅርና ለጠላት የማይንበረከክ መሆኑን በግልፅ ማሳየት ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here