የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት ስኬታማ ድል ማስመዝገባቸውን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡

438
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ

የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ በይፋዊ ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

<<እጅግ ስኬታማ ውሎ ነበረን፡፡ የክልላችን ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው ያሉ ዓመራሮች እና አባላት በተቀናጀ መልኩ ያደረጉት ተጋድሎ ስኬታማ ነበር፡፡ በትናንትናው ዕለት በሶሮቃ እና ቅራቅር ከዕኩለ ሌሊት እስከ ረፋድ ተደጋጋሚ ማጥቃት ተሰንዝሮብን ነበር፡፡ ከረፋድ በኋላ በሰነዘርነው ማጥቃት በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥረናል፡፡ በተቆጣጠርናቸው ቦታዎች ያለው የህዝብ ድጋፍ ድንቅ ነበር፡፡ በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የፀጥታ ኃይል በሰላም እጁን ሰጥቷል፡፡ እዋጋለሁ ብሎ የመረጠም ፊቱን አዙሮ እኛን ሲያግዝ ውሏል፡፡ ጦርነት አንፈልግም ስንል ጠላታችን ድህነት ነው ከሚል እንጅ ጦርነት ካለማወቅ አይደለም፡፡ ዛሬም በሌላ ድል ታጅቦ ያልፋል>> ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here