የመከላከያ ሕብረት ሎጂስቲክስ ሜንተናንስ መምሪያ በሕግ ማስከበር እና በኅልውና ዘመቻው የላቀ የሥራ አፈፃፀም ላላቸው ክፍሎች እና ግለሰቦች ዕውቅና እና የማዕረግ ማልበስ መርኃግብር አካሄደ፡፡

0
65

የካቲት 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሕብረት ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል አብዱራህማን ኡስማኤል ሜንቴናንስ መምሪያው በግንባር በመገኘት የጦር መሳሪያዎችን እና ከባድና ቀላል ተሸከሪካሪዎችን በመጠገንና ለግዳጅ ዝግጁ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡ ይህም በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

የመከላከያ ሜንቴናንስ መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል በርሄ ገብረ መድህን ፣ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ባደረሰው ጥቃት ምክንያት የሜንቴናንስ መሥሪያ ቁሳቁስ የተዘረፉና የወደሙ በመኾናቸው መምሪያው ችግሮችን እና ክፍተቶችን በመቋቋም ተንቀሳቃሽ ወርክ ሾፕን በየቦታው በማሰማራት፣ የጎደለውን የክፍሉን አመራርና ሙያተኛ በሟሟላት ሠርቷል፡፡

በማሰልጠኛ ማዕከላት ተተኪ የማፍራት ሂደቱ እንዳይስተጓጎል በማገዝ፣ የክፍሎችን የተኩስ አቅም ለማሳደግ ሙያዊ ፈጠራዎችን በመጠቀም መምሪያው አመርቂ ግዳጅ መፈፀም መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ሽልማቱ እንዳስደሰታቸው እና ለወደፊትም እንዲበረቱና ጠንክረው እንዲሠሩ የሚያደርግ መኾኑን ዕውቅና ያገኙ ተሸላሚዎች መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/