የመንግሥትን የክተት ጥሪ ተቀብለው ትግሉን ለመቀላቀል መዘጋጀታቸውን በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ።

0
66

የመንግሥትን የክተት ጥሪ ተቀብለው ትግሉን ለመቀላቀል መዘጋጀታቸውን በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ለጦርነት ብቁ የሆነ የግልና የመንግሥት የጦር መሳሪያ የታጠቁ ግለሰቦች ወደ ህልውና ዘመቻው እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

ጥሪውን ተከትሎም በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ የግልና የመንግሥት የጦር መሳሪያ የታጠቁ ግለሰቦቸ ትግሉን ለመቀላቀል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የግል ታጣቂው አቶ ክብረት አበራ ሀገር እንደ ሀገር እንድትቀጥል ሀገር ለማፈራረስ የተነሳውን የጁንታ ቡድን ለመደምሰስና የትኛውንም የሀገር ጠላት ለመመከት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የእናት ሀገርን የክተት ጥሪ ተቀብዬ ግንባር ለመዝመት የወጣሁት አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ብቻ ሳይሆን የእሱ ተላላኪ ባንዳዎችንም ከገጸ ምድር ለማጥፋት ነው ያሉት ደግሞ አቶ ይመር ከፋለ ናቸው።

ለሀገራችን ህልውና መስዋእት መክፈል ትልቁ ታሪክ ነው ያሉት አቶ አባቱ አዳነ ያለሀገር ሰላም መኖር አይቻልም ስለሆነም የአሸባሪውን የትህነግ ቡድን በመደምሰስ የሀገርን ክብርና ህልውና ለማስጠበቅ መነሳታቸውን ነው የተናገሩት።

ወጣት ፍስሃ ፈጠነ በበኩሉ በወያኔ የፕሮፖጋንዳ ቀረርቶ ሀገር አትፈርስም፤ ኢትዮጵያን ሲዘርፍ፣ ዜጎቿን ሲያንገላታና ትውልዷን በዘር ፓለቲካ ሲበትን የቆየው የትህነግ ቡድን የእናት ሀገሬን ዳር ድንበር፣ ሰንደቅ ዓላማና የዜጎቿን ክብር ዳግም ላይደፍር መልስ ለመስጠት መዘጋጀቱን ተናግሯል።

የመተማ ወረዳ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ተወከይ ኃላፊ አቶ ደርሶ ተገኘ ስግብግብ ጁንታውን ለመደምሰስ ወረዳው የጸጥታ መዋቅሩን በማደራጀት እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ኃላፊው አክለውም የክተት ጥሪውን ተከትሎ የሚሊሻ አባላት ወደ ግንባር ለመዝመት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ግንባር ለሚዘምተው የጸጥታ ኃይል ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡም ተጠቁሟል።

ዘጋቢ፡– ቴዎድሮስ ደሴ –ከመተማ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m