የመላው አማራ የስፖርት ውድድር ዛሬ በጎንደር አፄ ፋሲል ስታዲየም በወልቃይት ጠገዴና በራያ የስፖርት ቡድኖች ይጀመራል።

81
በከተማዋ የውድድሩ ማስጀመሪያ የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ተካሂዷል፡፡
ባሕር ዳር: መጋቢት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የመላው አማራ ስፖርት ውድድር ማስጀመሪያ መርኃ ግብር በከተማዋ ፒያሳ መስቀል አደባባይ በተካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎችና ለመላው አማራ ስፖርታዊ ውድድር ለመሳተፍ ከተለያዩ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የመጡ ስፖርተኞች፣ የቡድን መሪዎች እና አሰልጣኞች፣ የክልልና የፌዴራል የዘርፉ ባለሙያዎችና የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የማስጀመሪያ የአካል ብቃት እንቅስቃሴው የተካሄደው፡፡
በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አወቀ አስፈሬ ስፖርት ለጤንነትና ለሀገር ግንባታ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴርና የስፖርት ፌዴሬሽን የመላው አማራ የስፖርት ውድድር በከተማዋ እንዲካሄድ በመፍቀዳቸው እንዲሁም ተሳታፊ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ወደ ከተማዋ በመምጣታቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
May be an image of 7 people, people standing, footwear and outdoors
የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ እርዚቅ ኢሳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚያሳትፍ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤናን ለመገንባት፣ የተረጋጋ ኑሮን ለመምራት፣ ደስተኛ ሆኖ ለመኖር፣ በስፖርት ውድድሮች በተለይ ደግሞ በዓለም የስፖርት መድረክ አሸናፊ ለመሆን ያስችላል ብለዋል፡፡
አባቶቻችን ሀገራቸውን ከጠላት መከላከል የቻሉት ችግርን ተቋቁመው መዋጋት በመቻላቸው ነው ያሉት ዴኤታው የአሁኑ ትውልድም ሀገርን ከጠላት ለመከላከልና ለትውልድ ለማስተላለፍ በአካል በቅቶ ሊገኝ ይገባል ነው ያሉት፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ የከተማዋ ነዋሪዎች ለመላው አማራ የስፖርት ውድድር ለመሳተፍ የመጡ እንግዶችን በከተማዋ የእንግዳ ተቀባይነት ወግ አቀባበል እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከሚያዚያ 10 እስከ ሚያዚያ 24/2015 ዓ.ም በሚካሄደው የመላው አማራ የስፖርት ውድድር ዛሬ ከ6፡00 ስዓት ጀምሮ በአፄ ፋሲል ስታዲየም በወልቃይት ጠገዴና በራያ የስፖርት ቡድኖች መካከል እንደሚጀመር ከመርኃ ግብሩ መረዳት ተችሏል፡፡ መረጃው የጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!