የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

0
246

ባሕር ዳር፡ መስከረም 28/2013ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መሰብሰቢያ አደራሽ አካሂዷል፡፡

የኢፈዴሪ ፕሬዝዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን አዳምጧል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬ ስብሰባው የንግድ ሕግ ረቂቅ አዋጅን፣ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን፣ በኢትዮጵያ እና በራሽያ ፈዴሬሽን መንግሥት መካከል የኒውክሊየር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለማዋል የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን፣ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና ማስረጃ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን ዋልታ ዘግቧል፡፡

የምክር ቤቱን 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቁም ታውቋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here