የሀገር ባለውለታ ጀግኖችን ለትውልድ ማስተማርያነት መጠቀም እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

0
52
አዲስ አበባ፡ ሕዳር 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገር ባለውለታ ጀግኖችን መዘከርና ጀብዳቸውን አውቆ ለትውልድ ማስተማርያነት መጠቀም እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የሌተናል ኮሎኔል አብዲሳ አጋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መርቀዋል።
ከንቲባዋ እንዳሉት የሌተናል ኮሎኔል አብዲሳ አጋ ታሪክ የግለሰብ ሳይኾን የኢትዮጵያ ታሪክ ነው።
ለሀገሩ የታገለ የኢትዮጵያዊነት፣ የጀግንነት እና የጽናት ተምሳሌት ቢኾንም በልኩ አልተዘመረለትም ብለዋል።
ከንቲባ አዳነች ታሪክ የሠሩ ጀግኖችን በተምሳሌትነት ለትውልድ መማማርያ ልናደርግ ይገባል ነው ያሉት።
ሀገር መውደድን፣ ጀግንነትን እና አይበገሬነትን ከጀግናው በመማር ለሀገራችን ታሪክ መሥራት የዚህ ትውልድ የዜግነት ግዴታ እንደኾነም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ፦ በለጠ ታረቀኝ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!!