የሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ አናብስቶች የሜዳይና የእውቅና ሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት እየተከናወነ ነው።

0
137

ባሕር ዳር: የካቲት 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ አናብስቶች የሜዳይና የእውቅና ሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት በአፋር ሠመራ ከተማ እየተከናወነ ነው።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በህልውና ዘመቻው ላይ የላቀ ግዳጅ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የሠራዊቱ አባላት የሽልማትና እውቅና እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የኢፌዲሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ-ማርሻል ብርሃኑ ጁላና ምክትል ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል አበባው ታደሰ እንዲሁም የምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ፣ የአፋር ክልል ከፍተኛ አመራሮች ፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

የተሸላሚ ቤተሰቦችና የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ታድመዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/