የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ሉዓላዊነት ከማስከበር ባሻገር የልማት ሥራዎችን እያከናወነ ነው፡፡

44
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ

ወልድያ፡ መጋቢት 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የ801ኛ ኮር በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ቀዩ ጋሪያ ቀበሌ የተቀናጀ የጤና አገልግሎት መስጠት የሚችል ጤና ኬላ ለመገንባት የማስጀመሪያ ፕሮግራም አከናውኗል፡፡
ለግንባታው 10 ሚሊየን ብር ተመድቧል፡፡ በዚህ ዓመት ተጠናቆ በ2016 በጀት ዓመት ለአገግሎት እንደሚበቃም በዕለቱ ተገልጧል፡፡
የ801ኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ዘውዱ ሰጥአርጌ ሠራዊቱ ለራያ እና አካባቢው ሕዝብ የማኅረሰብ አግልግሎት መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
የራያ ቆቦ አሥተዳዳሪ ሞላ ደሱ፤ ሠራዊቱ በወረዳው የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ለአካባቢው ማኅበረሰብ ያለውን ፍቅርና አንድነት በተግባር እያሳየ መኾኑን አስረድተዋል ፡፡ ለዚህም የወረዳው ማኅበረሰብ ለሠራዊቱ ታላቅ አክብሮት እንዳለው አሥተዳዳሪው ገልጸዋል ፡፡
ዘጋቢ፦ባለ ዓለምየ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!