“የሀሰት መረጃ በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ያሳደረው ጫና እና መፍትሄው” የምክክር መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

100

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ “የሀሰት መረጃ በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ያሳደረው ጫና እና መፍትሔው” በሚል ርዕስ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
በምክክር መድረኩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሕበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሙሐዘ ጥበባ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ክቡር ዶክተር ኦባንግ ሚቶ እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
በምክክር መድረኩ የበቃ ዘመቻን ጨምሮ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ፣ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ በጦርነት ወቅት ታሪካዊ ዳሰሳ፣ የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙኀን የአፍሪካ ገጽታ እና ጫና በሚሉ ጉዳዮች ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
መረጃዎችን እየተከታተልን እናቀርባለን።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!