“ዘር ተኮር የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፅሞብናል” በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ከጥቃቱ የተረፉ አማራዎች

0
569
“ዘር ተኮር የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፅሞብናል” በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ከጥቃቱ የተረፉ አማራዎች
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 22/2013 (አብመድ) ትናንት ምሽት በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ቦኔ ቀበሌ በንጹሐን አማራዎች ላይ የጀምላ ጭፍጨፋ መፈፀሙን ከጥቃት የተረፉ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ትናንት ምሽት 1 ስዓት አካባቢ የታጠቁ የኦነግ ሸኔ አባላት ወደ ነዋሪዎቹ ቀየ ዘልቀው በመግባት ንጹሐን አማራዎች ላይ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል ነው ያሉት፡፡
ነዋሪዎቹ ከዚህ ቀድሞ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ሲዛትባቸው እንደነበር ገልፀው ትናንት ምሽት “ዘር ተኮር የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፅሞብናል” ብለዋል፡፡
ከምሽቱ 4 ስዓት ጀምሮ የጸጥታ ኃይል በአካባቢው ቢደርስም እርምጃ እንድንወስድ ስላልታዘዝን ራሳችሁን ጠብቁ በሚል ብቻ መመለሳቸውን ነግረውናል፡፡
አሁንም ተደጋጋሚ ግድያ ላለመፈፀሙ ምንም ዋስትና የለንም ያሉት ከጥቃት የተረፉ አስተያየት ሰጭዎቹ መንግሥት በአፋጣኝ ደርሶ እንዲታደጋቸው ጠይቀዋል፡፡
የኦሮምያ ክልል መንግሥት በአካባቢው በኦነግ ሽኔ ግድያ መፈጸሙን ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል፤ ጉዳዩን አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡን በተደጋጋሚ የደወልንላቸው የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እና ምክትል ኮሚሽነር ስልካቸውን ሊያነሱልን አልቻሉም፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here