ውሕደቱን ያጸደቁ የኢሕአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶች የብልፅግና ፓርቲን ፊርማቸውን በማኖር ተቀላቀሉ።

0
86

የብልፅግና ፓርቲን የተቀላቀሉ ድርጅቶች የስምምነት የፊርማ ሥነ ስርዓት ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ የኢሕአዴግና ኦዴፓ ሊቀ መንበር ዐብይ አህመድ (ዶክተር)፣ የአዴፓ ሊቀ መንበር ደመቀ መኮንን እና የደኢሕዴን ሊቀ መንበር ሙፈሪያት ካሚል ተገኝተዋል፡፡

ውሕደቱን ያጸደቁ ፓርቲዎች ሊቀ መናብርት፣ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

የብልፅግና ፓርቲ በእውነትና ዕውቀት ላይ ተመሥርቶ ኢትዮጵያን የሚያሻግር አስተማማኝ ድልድይ መሆኑን ዶክተር ዐብይ በሥነ ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል። ብልፅግና ፓርቲ ልማት እና ዲሞክራሲን ደምሮ የያዘ ፓርቲ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

ፓርቲው ግልፅ ፕሮግራም እና የሚመራበት ሕገ ደንብ ማዘጋጀቱን ዶክተር ዐብይ አህመድ መናገራቸውን ፋብኮ ዘግቧል፡፡

ፓርቲው ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና የሚያሸጋግር የ10 ዓመት መሪ እቅድ ማዘጋጀቱንም ገልጸዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here