ዋናው ውጤት በሕጉ መሰረት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደረጃ ስለሚገለጽ በማኀበራዊ ሚዲያ ጊዜያዊ ውጤቶችን የሚለጥፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ፡፡

0
108

ዋናው ውጤት በሕጉ መሰረት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደረጃ ስለሚገለጽ በማኀበራዊ ሚዲያ ጊዜያዊ ውጤቶችን የሚለጥፉ
አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 15/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሶሊያና ሽመልስ
በሰጡት መግለጫ ምርጫው በሰላም መጠናቀቁንና በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች መጠነኛ ችግሮች እንደገጠሙ ገልፀዋል።
ዳይሬክተሯ ትናንት በቁሳቁስ እጥረት ሳይካሄዱ የቀሩት የሲዳማና የጋምቤላ ክልል ምርጫዎች ዛሬ ችግራቸው ተፈትቶ ሲዳማ
ሙሉ በሙሉ ዛሬ ምርጫው ተካሂዶ ቆጠራው እየተካሄደ ነው ብለዋል።
በጋምቤላም በከፊል እየተከናወነ እንደኾነ ነው ያብራሩት።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት የምርጫ ክልሎች የኮድ ስህተት በማጋጠሙ ቁሳቁሱ እንዲቆለፍባቸው ተደርጓል ያሉት ወይዘሪት
ሶሊያና በቅርቡም ውሳኔ ይሰጣል ብለዋል።
እንደ ወይዘሪት ሶሊያና ማብራሪያ የድምፅ ቆጠራው በጣቢያዎች ደረጃ እየተጠናቀቀ ለሕዝብ እየተለጠፈና ወደ ምርጫ ክልሎች
እየተላከ ነው። እስካሁን ባለው በጊዜያዊ ውጤት ላይ የቀረበ ቅሬታ እንደሌለም ጠቁመዋል። ዋናው ውጤት በሕጉ መሠረት
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደረጃ ስለሚገለጽ በማኀበራዊ ሚዲያ ጊዜያዊ ውጤቶችን የሚለጥፉ አካላት ከድርጊታቸው
እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።
ፓርቲዎች የውጤት ገለፃ ሕጉን ተከትለው እየሠሩ በመኾናቸው ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
ቦርዱ ከየምርጫ ክልሎች የሚደርሱትን ውጤት በየጊዜው እንደሚገልጽም ተናግረዋል።
በካርተር ሴንተር አማካኝነት የመጡትና በመኝታ ክፍላቸው ሕይወታቸው አልፎ የተገኙት ግለሰብ ዓለም አቀፍ ታዛቢ ሳይኾኑ ቦርዱ
የልዩ እንግዳ መለዮ የሰጣቸው ነበሩ ብለዋል። ጉዳዩንም የጸጥታ አካላት እያጣሩት እንደኾነ ነው የገለጹት።
ዘጋቢ፡- ዘመኑ ታደለ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here