ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ አርቲስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ጥሪ አቀረበ፡፡

0
125
ጎንደር: ሕዳር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ በተካሔደው ❝የአንድነት ደወል ለኢትዮጵያ❞ የምክክር መድረክ የተገኘው አርቲስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ታማኝ በየነ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን #እንዲደመሰስ ሕዝቡ እምቢ ብሎ አሁንም መነሳት መቻል አለበት ብሏል። በዚህ ሀገር ፈተና በገባችበት ወቅት የአማራ ባለሀብቶች በትብብር እየሠሩ ያሉት ተግባር ደስ እንደሚያሰኝ ነው የገለጸው፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ እምቢ ብሎ የተነሳ ቀን የሚያቆመው ኃይል እንደሌለም ተናግሯል።
በጦርነት ውስጥ ገብቶ ከመፋለም ባሻገር ደጀን በመሆን ሠራዊቱን ማጠናከር እንዲሁም ወጣቶች የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።
በምክክር መድረኩ ላይ ለህልውና ዘመቻው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በተዘጋጀ የስዕል ጨረታ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል።
የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስን ስዕል ታዋቂው ባለሀብት አቶ በላይነህ ክንዴ በ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር አሸንፈው ወስደዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ስዕል ደግሞ ከወረታ ትሬዲንግ አቶ ታደሰ ምህረቴ በ3 ሚሊዮን ብር አሸንፈው ወስደዋል።
የዳግማዊ ምኒልክና የእቴጌ ጣይቱ ስዕል ለጨረታ ቀርቦ በ1 ሚሊየን ብር አቶ አለነ አድማሱ ወስደውታል።
አራተኛው የአፄ ፋሲል ግንብ ምስል ከባህሬን ትሬዲንግ ፀሐይ ቀለም በ2 ሚሊየን ብር የወሰዱ ሲሆን በመርኃግብሩ ላይ ከስዕሎች ጨረታ በጠቅላላ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል።
ዘጋቢ:- ፍፁምያለምብርሃን ገብሩ -ከጎንደር
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation